በአፋር በተለያዩ ወረዳዎች ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 24/2011) በአፋር የተሾመው አዲሱ አስተዳደር ምንም ለውጥ አላመጣልንም በሚል በተለያዩ ወረዳዎች ሰላማዊ ሰልፍ መካሄዱ ተሰማ።

ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጹት የወጣቱ ጥያቄ ለውጥ ይምጣ በአዲስ አመራር ኣነመራ የሚል ነበር።

ለዚህም ወጣቱ ለአዲሱ አስተዳደር የ100 ቀናት ጊዜን ሰጥቶ በመጠባበቅ ላይ ነበር ይላሉ ነዋሪዎቹ ።

ይሄ ደግሞ ወጣቱን ለቁጣ አነሳስቶታል ብለዋል።

በተለያዩ ወረዳዎች ላይ በአንድ ጊዜ ተደርጓል የተባለው ሰልፍ ምክር ቤት እስከ ማዘጋት ደርሷል ነው ያሉት ነዋሪዎቹ።

ይሄ ብቻ አይደለም ሰልፉ የተለያዩ አካባቢዎችንም በመዝጋት ተቃውሞውን ያሰማ መሆኑንም ገልጸዋል።

በአጠቃላይ 10 ወረዳዎችን አሳትፏል የተባለው ሰልፍ የኢትዮ-ጅቡቲ መንገድንም ቢያዘጋም ከሚያመጣው ጉዳት አንጻር ግን በስምምነት ተከፍቷል ብለዋል።

የወጣቱ ጥያቄ በዚህ ብቻ አያበቃም ያሉት ነዋሪዎቹ ነገም ሰልፉ በዚሁ መልኩ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

 

 

The post በአፋር በተለያዩ ወረዳዎች ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ appeared first on ESAT Amharic.


Source: ESAT